በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በሴቶች ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥተዋል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በሴቶች ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ያለዕድሜ ጋብቻ የሴት ልጅ ግርዛት ከልካይ ህጎችን በተመለከተ ከUNICEF ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባባር በዛሬዉ ዕለት የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ ማቴዎስ ማጃ ፣የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጣሰዉ ጨምረዉ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ ። ‎

‎ወላይታ ሶዶ፤ የካቲት 19/2018 ዓ/ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በሴቶች ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ያለዕድሜ ጋብቻ የሴት ልጅ ግርዛት ከልካይ ህጎችን በተመለከተ ከUNICEF ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባባር በዛሬዉ ዕለት የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ ማቴዎስ ማጃ ፣የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጣሰዉ ጨምረዉ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥተዋል ። ‎

‎በመድረኩ ላይ ተገኝተዉ የማጠቃላይ ሀሳብ የሰጡት የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ ማቴዎስ ማጃ :-ሴቶች በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ልንሰራ ይገባል ብለዋል ። ‎

‎በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰውን ጉዳትና እንግልት ለማስቀረት መንግስት በህግ በመደንገግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል። ‎ ‎የሴቶች እና ህፃናት መብት በዓለም አቀፍ ፤በሀገር አቀፍና በክልላዊ ህጎች ላይ የተደነገጉት መብቶችና አተገባበራቸዉ ላይ ክፍተት በመኖሩ ለማሻሻል ስልጠናው ለመስጠት ተፈልጓል ተብሉዋል። ‎ ‎ጠለፋ እና የመደፈር ወንጀሎችን እና የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ጋር በተያዘው እየቀረው የመጣ ብሆንም እንኳ በገጠርቱ አከባቢ አልፎ አልፎ የሚከሰተውን የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ላይ የህግ ክልከላ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ‎ ‎

የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጣሰዉ :_ እንደወረዳችን በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚደርሰው አደጋ ለመከላከል ብዙ ርቀት ሄደናል በማለት በዘላቂነት ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት አለበት።

‎በየደረጃው የተደነገገውን መብቶች እና አተገባበራቸዉ አንፃር ከአከባቢው አከባቢዉ የሚለይበት ሁኔታ ብኖርም ተቀራራቢነት ስለሚኖረው ግንኙነት አገባብ ማሻሻል አለበት።

‎የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የፍትሃ ብሔር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ዐቃቤ ህግ አቶ ታከለ በቀለ በበኩላቸው :-ሴቶች እና ህፃናት መብት በህግ በተደነገገው መሰረት ተግባራዊ እንድሆን በትኩረት መስራት አለበት። ‎

‎የሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ይበልጥ በማሳደግ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን አሻራ እስኪያስቀመጡ ማገዝና ማብቃት የሁሉም ሰው ኃላፊነት ልሆን ይገባል። ‎ ‎የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ አስተዳደር ተወካይ አቶ ማቴዎስ ማጃ ፣የቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጣሰዉ ጨምረዉ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው